ቡቃያ
 ትምህርታዊ የልጆች እና የቤተሰብ መጽሔትማውጫ


ቡቃያ ምንድነው?

በዐማርኛ ቋንቋ የሚዘጋጅ የቤተሰብ መጽሔት ነው
መጽሔቱ የሚከተሉትን ተግባሮች እንደ ዐላማዎቹ ይቈጥራቸዋል፤

ቡቃያ የተሟላ የዐማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ አይደለም። ከዐላማዎቹ ዋነኛው ግን ለመምህራን፣ ለወላጆች፣ ለአሳዳጊዎች እና ለማኅበረሰብ ማእከሎች (ኮምዩኒቲ ሴንተርስ) ስለ ልጆች ማስተማሪያ ዘዴዎች መንደርደሪያ ሐሳብ ማቅረብ ነው። ቋንቋን በቅልጥፍና እና በቀላሉ ለልጆች ማስተማር የሚቻለው ፊደል የማስቈጠር ተግባር ተረቶች በመተረክ፣ ድርሰቶች በማንበብ፣ መዝሙሮች በማስጠናት፣ የቃላት ጨዋታዎችን እና እንቆቅሎችን ከልጆች ጋር ዐብሮ በመጫወት፣ ሥዕሎችን በልጆች አንደበት እንዲገለጹ በማበረታታት፣ እንዲሁም በሌሎች የማስተማሪያ ዘዴዎች ሲታገዝ ነው።

ቡቃያ ለማን?

- መጽሔቱ ከባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልጆች ጥቅም እና ፍላጎት ቀዳሚ ትኵረት ቢያደርግም፣
- ለወላጆቻቸው እና ዐማርኛ መማር ለሚፈልጉ ጐልማሶች ኹሉ አገላጋይ እንዲኾን የተቻለውን ያደርጋል።
- ለወላጆች እና ሌሎች ጐልማሶች የቋንቋቸው፣ የባህላቸው እና የልጅነታቸው አስታዋሽ ለመኾን ይሞክራል።
- በተለይ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ትምህርት-አዘል ማለፊያ ጊዜ (ኳሊቲ ታይም) እንዲኖራቸው አጋጣሚዎች መፍጠር ይፈልጋል።

ባጭሩ ቡቃያ ቤተሰብን ለማገልገል የሚዘጋጅ መጽሔት ነው።


ካለፉ ዕትሞቻችን

ስለ መጽሔታችን ይበልጥ ልመረዳት የሚከተሉትን ካለፉ የቡቃያ ዕትሞች የተቀነጨቡ ናሙናዎች (ሳምፕልስ) ይመልከቱ።

የቍጥር 4- ቃላት ሰንጠረዥ
የቍጥር 3 - ቃላት ከበባ
የቍጥር 6 - ማዛመድ
የቍጥር 7 - ሥዕል ከቃል ማዛመድ
የቍጥር 9 - መስቀልኛ ቃላት
የቍጥር 7 - ተረት ተረት - ስልጆ
የቍጥር 5 - የልጆች መዝሙር - ላንዲሮ
የቍጥር 1 - ባህል እና ወግ - ስለ ቡሔ አፈ-ታሪክ

ያለፉ ዕትሞችን ለመግዛት

ቡቃያ በኹለት ዓመታዊ ቅጾች የተጠቃለሉ 16 ዕትሞችን አውጥቶ ለአንባቢያን አቅርቦ ነበር። እኒህ ዕትሞች ተሽጠው በማለቃቸው የግዢ ትእዛዝ መቀበል አቁመናል። ዕትሞቹ የወጡበት ጊዜ ካለፈ በጣም ቢቆይም ይዘቶቻቸው ሰሞናዊ (ለተወሰነ ዐጭር ጊዜ የሚያገለግል) አልነበረም። ስለዚህም የዕትሞቹን ይዘት በአንድ ጥራዝ አጠቃልሎ የማውጣት ዕቅድ አለ። ይህን ጥራዝ መግዛት የሚፈልጉ ከኾነ እባክዎ ስምዎን፣ የፓስታ እና የኤ-መልክት አድራሻዎችዎን ያሳውቁን። ጥራዙ ታትሞ የሚወጣበት ጊዜ የተረጋገጠ ሲኾን ይህንኑ እናሳውቅዎታለን።


ይጻፉልን

የቡቃያ አዘጋጆች አስተያየት እና ምክር ለመስማት፣ ጥያቄ ለማስተናገድ፣ የፈጠራ እና የተመክሮ ጽሑፎች ገምግሞ ለአናባቢያን ለማቅረብ ዝግጁ ነን። እንዲያውም ያለ አንባቢያን ንቁ ተሳትፎ መጽሔቱ እድገት እና ዘላቂነት እንደማይኖረው እናምናለን። ስለዚህ የሚያውቋቸውን ተረቶች፣ መዝሙሮች፣ ጨዋታዎች፣ የልጅነት ገጠመኞች ይጻፉልን። በዐማርኛ ወይም በሌላ የኢትዮጵያ ቋንቋ፣ አሊያም በእንግሊዝኛ ሊጽፉልን ይችላሉ። በተቻለ መጠን መተርጐም ያለበትን ወደ ዐማርኛ መልሰን ልናሳትምልዎ እንሞክራለን።

E-mail: bukaya@hahubooks.co.uk


በተጨማሪ የእንግሊዝኛውን ገጽ ይመልከቱ።